Fana: At a Speed of Life!

የትኛውም ኃይል የህዳሴ ግድብ ግንባታን ማስቆም አይችልም – የምዕራብ ዕዝ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር እንዲሳለጥ የምዕራብ ዕዝ ፈርጀ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የዕዙ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ተመስገን ገለፁ።

ጀኔራል መኮንኑ በግድቡ አካባቢ ፀጥታን የማረጋገጥ ስራዎች በመስራት ላይ የሚገኙትን የሰራዊት አባላት በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት፥ “የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደ ሀገር ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ህዝባችን ፍፃሜውን በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተለውን ይህን ፕሮጀክት ሰራዊታችንም በንቃት እየጠበቀው ይገኛል” ብለዋል፡፡

የፀጥታ ስራውን ይበልጥ ለማጠናከር የዕዙ ኮማንድ ያልተቋረጠ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ጀነራል መኮንኑ፥ የግንባታ ሒደቱን በቅርበት የሚከታተለው ሰራዊቱ ውጤቱን እየተመለከተ ስለሚገኝ ለተሰጠው ተልዕኮ እንደ ተደማሪ አቅም ሆኖታል ነው ያሉት፡፡

ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ የትኛውም ኃይል የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግንባታን ማስቆም እንደማይችል ጠቁመው፥ ሰራዊቱ በከፍተኛ እልህና ሞራል የተጣለበትን ሃላፊነት ከመወጣት ባሻገር ለሰባተኛ ጊዜ በወር ደመወዙ የቦንድ ግዥ መፈፀሙን እንደተናገሩ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.