Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ሀገር አቀፍ የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ትስስር ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ።

ጉባኤው እየተካሄደ ያለው “እውቀት መር አመራርነት ለላቀ የፀረ ሙስና ትግል” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

በመድረኩ የዘርፉ ሀገር አቀፍ የ2016 አመታዊ መሪ ዕቅድ መቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይ በፀረ ሙስና ትግል እንቅስቃሴ ላይ የህዝብ አስተያየት ለማወቅ የተከናወነ የዳሰሳ ጥናት እና የተቋማዊ አደረጃጀት ገለልተኝነትና ብቃትን ለማሻሻል የተከናወነ ጥናት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ለአንድ ቀን በተዘጋጀው በዚሁ ጉባኤ ላይ የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ እና የሁሉም ክልሎች የዘርፉ ኮሚሽነሮች ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.