ስፓርት

አትሌት አማኔ በሪሶ በሴቶች ማራቶን የወርቅ ሜዳልያ አስገኘች

By Feven Bishaw

August 26, 2023

 

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በውድድሩ አትሌት አማኔ በሪሶ 1ኛ በመሆን ስታጠናቅቅ አትሌት ጎይተቶም ገብረስላሴ 2ኛ በመሆን የብር ሜዳልያ አስገኝታለች።

አትሌት አማኔ በሪሶ ርቀቱን 2 ሰአት ከ24 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ስታጠናቅቅ አትሌት ጎይተቶም 2 ሰአት ከ24 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ በመግባት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።