Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴር 4 ትራክተሮችን እና 91 የውሃ ፓምፖችን ለትግራይ ክልል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር 4 ትራክተሮችን እና 91 የውሃ ፓምፖችን ለትግራይ ክልል ድጋፍ አድርጓል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)በትግራይ ክልል ደቡብ ምስራቅ ዞን እንደርታ ወረዳ በምርት ዘመኑ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ከክልልና ከዞን አመራሮች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በጉብኝቱ የአርሶአደሩ መነቃቃት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልፀው የግብርና ሚኒስቴር አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

አርሶአደሩ የእርሻ ልማት ስራን ጨምሮ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንዲሁም በእንስሳት ልማት ዘርፍ ላይ የተለያዩ ልማቶችን እያከናወነ መሆኑንም በጉብኝታቸው ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል የደቡብ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ ወ/ሮ ሊያ ካሳ በበኩላቸው÷ በደቡብ ምስራቅ ዞን በዚህ አመት በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የታዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ስራውን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ክልሉን ለመርዳት ሁሉም ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡና እቅዳቸውን እንዲያጠናቅቁ ከማድረግ ጎን ለጎንም የቀሩ ስራዎችን የመለየት ስራ ተሰርቷል ነው ያሉት፡፡

ግብርና ሚኒስቴር በክልሉ ያለውን የግብዓት አቅርቦትና የመሰረተ ልማት ችግርን ከመቅረፍ ጎን ለጎን የመካናይዜሽን ስራዎችን ለማጠናከር ትራክተሮችን ጨምሮ የተለያዩ የቢሮቁሳቁስ እገዛዎችን ሲያደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

አሁንም ሚኒስቴሩ 4 ትራክተሮችን እና 91 የውሃ ፓምፖችን በክልሉ ለሚካሄደው የግብርና ልማት ስራ እንቅስቃሴ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በመጨረሻም በክልሉ የ2015 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም እና በ2016 በጀት አመት እቅድ ዙሪያ ውይይት መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.