በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሚሊዮን አለፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሚሊዮን አለፈ፡፡
በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሚሊዮን ሰዎች በላይ መያዛቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመለክታል፡፡
በቻይናዋ ዉሃን ግዛት መነሻውን ያደረገው ወረርሽኝ ለአለም የጤና ድርጅት ሪፖርት ከተደረገበት አራት ወራት ውስጥ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባዋል፡፡
በአለም በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርም ከ277 ሺህ በላይ ሆኗል፡፡
በአለም በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ያሉባት ሃገር አሜሪካ ስትሆን ከ1 ሚሊዮን 309 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡
ሆኖም ባለሙያዎች እንደሚሉት በአንዳንድ ሃገራት የሚመረመሩ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከዚህ ይልቃል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ