Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ በ”ብሪክስ”ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰሚነቷ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል – የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ለ”ብሪክስ” አባል ሀገራት ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ በቡድኑ ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰሚነቷ እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ እንደሆነ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ገለጸ፡፡

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎም የክልሉ መንግስት መግለጫ ሠጥቷል፡፡

ክልላዊ መንግስቱ በመግለጫው ፥ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለችው ፈጣንና ዘላቂ ምጣኔ ሃብታዊ እመርታ ከዓለም ሀገራት ጋር ያላት ወንድማማችነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጎለብት ብሎም ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ አስችሏል ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ ካቀረቡ 40 ሀገራት መካከል አንዷስትሆን የአባልነት መስፈርቱን አሟልታ ተቀባይነት ማግኘቷ ደግሞ ሀገሪቷ ያሸነፈችበት ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል መሆኑንም አስፍሯል፡፡

በዲፕሎማሲው በኩል የተገኘው ድል በኢንቨስትመንት እና በወጪ ንግዷ ኢትዮጵያን ቀጥታ የቡድኑ አባል ሀገራት ቀዳሚ ተመራጭ እንድትሆን እንደሚያስችላትም የክልሉ መግለጫ አውስቷል።

ኢትዮጵያ ከአባል ሀገራቱ እንዲሁም ከዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጋር የሚኖራት ግንኙነት ተጠናክሮም የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር እንደሚሰፋ ይኅም ለሀገሪቷ የብልፅግና ጉዞ ማፋጠን ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መግለጫ ÷ የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሀገሪቷ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንዲጎለብት ሁሉም የአካባቢውን ሠላም በመጠበቅና ዘላቂ ደኅንነት በማረጋገጥ የበኩል ሚና እንዲወጣም አሳስቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.