ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 29 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል
አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 02፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሠዓታት ውስጥ 2 ሺህ 171 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ29 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 21 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንኪኪ ያላቸው ናቸው።
ስምንቱ ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 239 ደርሷል
ቫይረሱ በምረማራ የተገኘባቸው ሰወች ሁሉም ወንድ ኢትዮጲያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ15-45 ዓመት የሆኑ ናቸው ፡፡
ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 21 ሰወች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 7 ሰወች ከሶማሌ ክልል (ሶማሌ ለይቶ ማቆያ) እና አንድ ሰው ከኦሮሚያ ክልል (አዳማ ከተማ በቤት ለቤት አሰሳ እና ቅኝት የተለየ) ይገኛሉ፡፡
ከበሽታው አዲስ ያገገሙ ሰወች ሁለት ሲሆኑ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰወች ቁጥር 99 ደርሷል፡፡
እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸውን ያጡ ሰወች ቁጥር አምስት ናቸው፡፡