ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 29 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 02፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሠዓታት ውስጥ 2 ሺህ 171 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ29 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 21 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንኪኪ ያላቸው ናቸው።
ስምንቱ ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 239 ደርሷል።
ቫይረሱ በምርማራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ እድሜያቸው ከ15 እስከ 45 ዓመት የሆኑ ናቸው ፡፡
ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 21 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ 7 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ከሶማሌ ክልል ለይቶ ማቆያ) እና 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (አዳማ ከተማ በቤት ለቤት አሰሳ እና ቅኝት የተለየ) ይገኛሉ፡፡
ከበሽታው አዲስ ያገገሙ ሰዎች ሁለት ሲሆኑ፥ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 99 ደርሰዋል፡፡
እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር አምስት ናቸው፡፡