ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከቤልጂየም ንጉስ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከቤልጅየም ንጉሥ ፊሊፕ ሌኦፖልድ ሉዊ ጋር በስልክ ተወያዩ።
ፕሬዚዳንቷ ከንጉሱ ጋር ሁለቱ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እያደረጉት ስለሚገኘው ጥረትን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ወረርሽኙ የሚሸነፈው ሀገራቱ በትብብር ሲቆሙ መሆኑን መሪዎቹ ገልፀዋል።