Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ተወላጅ ባለሐብቶች በክልሉ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ተወላጅ ባለሐብቶች በክልሉ ባለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የክልሉ መንግሥት ጥሪ አቀረበ፡፡

በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን የተመራ ልዑክ በኬንያ ከሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ጋር በክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡

አቶ ኢብራሂም በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው ሠላምና ልማት በማኑፋክቸሪንግ፣ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ልማት፣ በግብርና እንዲሁም በተለያዩ የንግድ ሥራዎች ላይ በርካታ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

የክልሉ ተወላጅ ኢንቨስተሮችና የንግዱ ማኅበረሰብ አባላትም በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ ባለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኬላቸው÷ በክልሉ በኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.