ቢዝነስ

ባለፉት አስር ወራት ውስጥ ከ198 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

By Tibebu Kebede

May 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2012 በጀት ዓመት አስር ወራት ውስጥ 198 ቢሊየን ብር 477 ሚሊየን 959 ሺህ ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።

በ2012 የበጀት አመት ከ270 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። በዚህም ባለፉት አስር ወራት ሲሆን በ10 ወር ውስጥ 198 ቢሊየን ብር 477 ሚሊየን 959 ሺህ ብር ገቢ በመስብሰብ የአመቱን ዕቅድ 73 ነጥብ 5 በመቶ ማሳካት መቻሉን ነው የተነገረው።