ስፓርት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ

By Mekoya Hailemariam

August 29, 2023

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈወ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም÷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 4 የብርና 3 ነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ማግኘቷ ይታወቃል።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ሆና ማጠናቀቋም የሚታወስ ነው።