የቻይና -አፍሪካ የእውቀት ሽግግር ሲምፖዚየም በቤጂንግ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና -አፍሪካ የእውቀት ሽግግር ሲምፖዚየም በቤጂንግ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በቤጂንግ እየተካሄደ በሚገኝው ሲምፖዚየም ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስር ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ኢትዮጵያን በመወከል ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸውም ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ ከቻይና ጋር ያላት የንግድና የወጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የሁለቱ ወገን የጋራ ተጠቃሚነትና ትብብር እያደገ መምጣት ችሏል ብለዋል።
አክለውም እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የቢዝነስ ዲፒሎማሲ ላይ ትኩረት ተደርጎ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሲምፖዚየሙ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ፥ የኢትዮጵያን ወጪ ምርቶች ገበያ ለማስፋት የሚያስችል የሁለትዮሽ የጎንዮሽ ውይይቶች እንደሚካሄዱ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!