Fana: At a Speed of Life!

የቢል ኤንድ ሚልንዳ ጌትስ ፋዉንዴሽን ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቢል ኤንድ ሚልንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዓለም አቀፍ ልማት ፕሮግራም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ግብን ለማሳካት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

በቦትስዋና እየተካሄደ ከሚገኘው 73 ኛው የአፍርካ አህጉር የዓለም ጤና ድርጅት መድረክ ጎን ለጎን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ከቢል ኤንድ ሚልንዳ ጌትስ ፋዉንዴሽን ዓለም አቀፍ ልማት ፕሮግራም ፕሬዚዳንት ዶክተር ክርስቶፈር ኤልያስ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የእናቶችና ሕጻናትን ሞት ከመቀነስ እንዲሁም በሽታን በመከላከልና መቆጣጠር ረገድ ያስመዘገበችውን አመርቂ ውጤቶች ዶክተር ደረጀ በውይይታቸው ላይ አብራርተዋል፡፡

የክትባት አገልግሎትና ቤተሰብ ዕቅድን ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንጻር ሚልንዳ ጌትስን ጨምሮ የአጋር ድርጅቶች ድርሻ ጉልህ መሆኑን ጠቅሰው÷ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በተለይም ከአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ እየተከሰቱ ያሉ እንደ ኮሌራ፣ የወባ በሽታ እና ሌሎች ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በክትባት የምንከላከላቸውን እንደ ኮሌራ፣ ኩፍኝ፣ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር እና ፓልዮ በሽታን ለመከላከል ሚልንዳ ጌትስ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ያሉት ዶ/ር ደረጀ÷ ወቅታዊነቱን የጠበቀ ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር ድጋፉ እንዲጠናከር ጠይቀዋል፡፡

ዶክተር ክርስቶፈር ኤልያስ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የእናቶችና ሕጻናት ጤናን በማሻሻል ወረርሽኞችን ጨምሮ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር ላይ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት ማስገኘቱን ገልጸዋል፡፡

የክትባት አቅርቦትን በማሳደግ፣ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የሚሰራውን የቅኝትና ቁጥጥር ስራ፣ የህብረተሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎ ለማሳደግ እንዲሁም በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ላይ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.