ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የወጪ ንግድ ትስስር ለማሻሻል እየተሰራ ነው – ሚኒስቴሩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የወጪ ንግድ ትስስር ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የቻይና-አፍሪካ የእውቀት ሽግግር ሲምፖዚየም በቻይና ቤጂንግ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የተሳተፉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ÷በቻይና የኢትዮጵያ ምርት ገዢ ከሆኑ ታላላቅ የቅባት እህል ተቀባይ ነጋዴዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት መደረጉን አንስተዋል፡፡
ቻይና የኢትዮጵያ ወጪ የግብርና ምርቶችን በመቀበል ቀዳሚ መሆኗን ጠቁመው÷ በሀገራቱ ንግድ ልውውጥ ላይ የተስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡
በሚቀጥሉት ወራት ከቻይና ጋር የሚኖው የወጪ ንግድ መሻሻል እንደሚያሳይ እምነታቸው መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡