Fana: At a Speed of Life!

የዩክሬን ድሮኖች ሩሲያ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸማቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሥድስት የሩሲያ ክልሎች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ማድረሳቸው ተነገረ፡፡

ዩክሬን በምዕራባዊው ፕስኮቭ ከተማ በሚገኘው የሩሲያ አውሮፕላን ማረፊያ በፈጸመችው ጥቃትም ወታደራዊ ማመላለሻ አውሮፕላኖች ላይ ጉዳት ማድረሷን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ÷ ዛሬ ዩክሬን የፈጸመችብን የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ከባለፈው ዓመት ወዲህ ትልቁ ነው ሲል ሁኔታውን ገልጾታል፡፡

አክሎም በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ዙሪያ እና በኦርሎቭ ፣ ብራያንስክ ፣ ራያዛን እና ካሉጋ ክልሎች ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትተን ጥለናል ብሏል፡፡

ሩሲያም በወራት ዕድሜ ውስጥ እጅግ ከባድ ነበር የተባለለትን የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት በዩክሬኗ ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ መፈጸሟ ተነግሯል፡፡

የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ በቴሌግራም በፃፉት መልዕክት ÷ በጥቃቱ ሁለት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን እና አንድ ሰው መቁሰሉን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.