ዳግም ያገረሸው የደቡብ ኮሪያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ፈጥሯል
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዳግም እያንሰራራ መሆኑ ተነገረ።
በሀገሪቱ ዛሬ ብቻ 35 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸው፤ በአጠቃላይ በ48 ሰዓታት ውስጥ በሀገሪቱ 69 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ነው የተገለፀው።
አብዛኛዎቹ ሰዎችም ቫይረሱ ያገኛቸው በመዲናዋ በሚገኙ የምሽት ዳንስ ቤቶች እና ባሮች መሆኑ ተመልክቷል።
እስካሁን 4 ሺህ ሰዎች በእንደነዚህ ሰፍራዎች ላይ የነበሩ ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን፥ ቀሪ 3 ሺህ ሰዎችን የማሰሱ ስራ መቀጠሉ ተገልጿል።
የሀገሪቱ መንግስትም ዋና ትኩረቱ እነዚሀን ሰዎች አድኖ በመያዝ ምርመራ ማድረግ መሆኑን አስታውቋል።
በተመሳሳይ በቻይናም አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ነው የተሰማው።
ባለፉት ሰዓታት ሀገሪቱ 17 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ስትገልፅ ከእነዚህ ውስጥ አምስቱ በዉሃን ግዛት የሚገኙ የአንድ መንደር ሰዎች ናቸው።