ጠ/ሚ ዐቢይ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር በስልክ ተወያዩ።
በውይይታቸው ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟን እና ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል እንደገለጹላቸው በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ፈታኝ ወቅት የኢትዮጵያ አጋሮች ወሳኝ የድጋፍ ምንጭ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በውይይቱም አብሮ የመቆምን ጠቀሜታ በተጨባጭ መመልከታቸውንም አንስተዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።