Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ27 ሺህ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ 2015 በጀት ዓመት 27 ሺህ 768 ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዕቅዱን 95 በመቶ ማሣካት መቻሉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምከክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱሠላም ሸንገል÷ ተቋሙ ለዜጎች ዘላቂና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል የ10 ዓመት ዕቅድ አዘጋጅቶ እየተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመት ለ29 ሺህ 164 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ 27 ሺህ 768 ለሚሆኑት ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዕቅዱን 95 በመቶ ማሣካት መቻሉንም አስረድተዋል።

በ2015 በጀት ዓመት በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች ለዜጎች የተፈጠረው የሥራ ዕድል ከ2014 ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ4 በመቶ ዕድገት አሣይቷል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ከተፈጠረው የሥራ ዕድል ውስጥ የሴቶች ድርሻ 26 በመቶ መሆኑንም አንስተዋል።

በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑንም አቶ አብዱሠላም መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ መላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.