Fana: At a Speed of Life!

የዋይት ሃውስ ሰራተኞች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ ተቋሙ ሰራተኞቹ ላይ የፊት ማስክ የመጠቀም ግዴታ ጣለ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በዩናይትድ ስቴትስ በሁለት የዋይት ሃውስ ሰራተኞች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ ተቋሙ ሰራተኞቹ ላይ የፊት ማስክ የመጠቀም ግዴታ ጣለ።

ዋይት ሃውስ እንዳስታወቀው የትኛውም ሰራተኛ ወንበሩ ላይ ሲቀመጥ ካልሆነ በስተቀር በየትኛውም እንቅስቃሴው ላይ የፊት መሸፈኛ መጠቀም ግዴታው ነው ብሏል።

መመሪያው እንዲወጣ አዝዣለሁ ያሉት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ምንም ዓይነት የፊት መሸፈኛ ሳይጠቀሙ በግቢው ውስጥ ከጋዜጠኞች ፊት ቆመዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከሁሉም ሰው ርቀታቸውን ጠብቀው ያሉ በመሆናቸው ስጋት እንደሌለባቸው ነው የተናገሩት።

በዋይት ሃውስ የምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ፕረስ ሰክረተሪ እና የፕሬዚዳንት ትራምፕ ባለቤት ረዳት የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ሌሎች ሶስት የኮሮና ቫይረስ ግብረሃይል አባላት ደግሞ ምናልባት ለቫይረሱ ተጋልጠን ከሆነ በሚል ራሳቸውን አግልለዋል።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.