Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሰንደቋን ከፍ የሚያደርጉ የጸጥታ ሃይሎችና ዜጎች አሏት – የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ ባሳለፈቻቸው ወቅቶች የተለያዩ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ሰንደቋን ከፍ የሚያደርጉ የጸጥታ ሃይሎችና ዜጎች እንዳሏት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመለከተ።

በኮሚሽኑ ”በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር ” በሚል መሪ ሐሳብ ውይይት እና ምክክር እየተካሄደ ነው።

መስዋዕትነት ሀብት እና እውቀትን ለሀገር ክብር በማካፈል በጎ ዋጋን ማሳየት መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።

የመስዋዕትነት ቀን ሲከበር የሀገር ዳር ድንበርን በመጠበቅ ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ ሀገርን ያቆዩ ጀግኖች አባቶችን በማሰብ መሆን እንዳለበትም ነው የተገለጸው።

ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ ባሳለፈቻቸው ወቅቶች የተለያዩ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ሰንደቋን ከፍ የሚያደርጉ የጸጥታ ሃይሎች እና ዜጎች እንዳሏት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሕግ እና ሰብዓዊ መብት መምርያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ፋሲል አሻግሬ ተናግረዋል።

ሀገር ነጻነቷ እና ታሪኳን የጻፈችው መስዋዕትነት ተከፍሎ በመሆኑ አሁንም በጀግኖች ልጆቿ ዋጋ ተከብሮ ለማቆየት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባም ረዳት ኮሚሽነሩ አንስተዋል።

በመድረኩ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት እና አመራሮች ተሳትፈዋል።

በለይኩን ዓለም እና ፍቅረሚካኤል ዘየደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.