Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነጻነት መጠበቅ በየዘመኑ ጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነትን ከፍለዋል – ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነጻነት መጠበቅ በየዘመኑ ጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነትን ከፍለዋል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ ገለጹ።

በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር በሚል መሪ ሀሳብ ጳጉሜ 2 የሚከበረውን የመስዋትነት ቀን አስመልክቶ የሃይማኖት አባቶች፣ ማህበራዊ አንቂዎች፣ የጸጥታ ተቋማትና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ በቀረቡ ጽሁፎች የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የተጠበቀው በመስዋዕትነት እንደሆነና ምክንያታዊ ትውልድ መፍጠር እንደሚገባ ተገልጿል።

በፓናሉ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ የረጅም ጊዜ የስልጣኔ ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ቅብብሎሽ ትቀጥላለች ሲሉ ተናግረዋል።

ሉዓላዊነቷ ተደፍሮ ነጻነቷም ተገፎ እንደማያውቅ ጠቅሰው፤ ለዚህ ሉዓላዊነትና ነጻነት ደግሞ በየዘመኑ ጀግኖች ልጆቿ መስዋትነትን ከፍለዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ቅብብሎሽ ትቀጥላለች ሲሉም ገልጸዋል።

በመከላከያ ሰራዊት የስነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን በበኩላቸው፤ የህዝብ ልጅ የሆነው መከላከያ መስዋእትነት እየከፈለ ኢትዮጵያን እንደሚጠብቅም አረጋግጠዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ የውይይት መነሻ ጽሁፎች ያቀረቡት ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ እና ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የተጠበቀው በመስዋትነት እንደሆነ አንስተዋል።

ነገር ግን ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ዋጋ የከፈሉ የጸጥታ አካላት በሚገባው ልክ እንዳልተዘመረላቸው ገልጸዋል።

በተለይ በዚህ ዘመን ምክንያታዊ ትውልድ መፍጠር ላይ መረባረብ እንደሚገባም አመላክተዋል።

የፓናሉ ተሳታፊዎችም ኢትዮጵያ የሰው ልጅን ክብርና እኩልነት ቀድማ በመረዳት ለብዙዎች ነጻነት አርአያ የሆነች ሀገር መሆኗን ማንሳታቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው።

የመከላከያ ሰራዊቱ ራሱን ለሀገርና ህዝብ በመስጠቱ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እሴትና ትውፊቶች ሳይሸራረፉ እንዲቆዩ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.