ከፍተኛ የደም ግፊት መንስዔዎችና መከላከያ መንገዶች
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የደም ግፊት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል የጤና እክል ነው፡፡
ከነዚህ ምክንያቶች መካከልም ዘር፣ ዕድሜ፣ አልኮል መውሰድ፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት፣ በአንዳንድ የጤና እክሎች እንዲሁም አጋላጭ ሁኔታዎች ይከሰታል፡፡
በደም ስር ውስጥ የሚተላለፈው የደም መጠን ከፍተኛ መሆን ለደም ግፊት በሽታ ተጋላጭ ያደርጋል፡፡
በረጅም ጊዜ ውስጥ የደም ግፊት መጨመር የልብ ሕመምን ጨምሮ ለሌሎች የጤና ችግሮች መከሰት መንስዔ ሊሆን እንደሚችልም የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
የደም ግፊት ብዙውን ጊዜ በርካታ ዓመታት ሣይታወቅ ወይንም ምልክቶች ሣያሳይ ሊቆይ ቢችልም እንኳን ከፍተኛ የደም ግፊት በደም ስር፣ በአንጎል፣ በልብ፣ በዓይንና በኩላሊት ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም ይገለጻል።
ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ምልክቶች መካከል ፊት ላይ ወይም ሌሎች የሰውነት አካል ላይ የመቅላት፣ በአይን ውስጥ የደም ነጠብጣቦች መኖር እና ድባቴ ውጥ መግባት ይጠቀሳሉ፡፡
እነዚህ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት መደበኛ የሆነ የደም መለካት እና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ኸልዝላይን ይመክራል፡፡
ሆኖም የደም መለካት ብቻውን መፍትሄ ባለመሆኑ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ከከፍተኛ የደም ግፊት ብቻ ሣይሆን ከአብዛኛው ሕመም ለመጠበቅ ወደር የሌለው መፍትሄ እንደሆነም ይነገራል፡፡
እንደ አብነትም፡-
• ፍራፍሬ፣ አትክልቶችን፣ ያልተፈተገ ሥንዴ እና እንደ ዓሳ ያሉ በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፤
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባሕል ማድረግ የልብና፣ የደም ዝውውር ሥርዓትን በማሻሻል እንዲሁም መጠነኛ የሰውነት ክብደት እንዲኖር በማድረግ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ እንዲከተሉ ያደርጋል፤
• ጭንቀትን ማስወገድ፤
• አልኮል እና ሲጋራ ማጨስን ማስወገድ፤
• ስኳር እና ጨው የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ ወይንም አለመውሰድና ሌሎች መፍትሄዎችን በመውሰድ ከከፍተኛ የደም ግፊት ራስዎን መከላከል እንዲሁም መቆጣጠር እንደሚገባ የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
ከዚህ አለፍ ብሎ ከፍተኛ የደም ግፊት ሕክምና መውሰድ ቢኖርብዎ በሐኪም ብቻ የታዘዙ መድሃኒቶች መውሰድ እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ያስፈልጋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!