Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከ424 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ424 ሺ 689 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች በዛሬው እለት ማዕድ አጋርተዋል።

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ዛሬ ከ424 ሺህ በላይ የሚሆኑ አቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎች እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሠራተኞች አዲሱን ዓመት በደስታ እንዲቀበሉ ማዕድ በማጋራት የበጎነት ቀንን ማክበር ጀምረናል ብለዋል።

በበጎ ፈቃድ ስራዎች የነዋሪውን ዕርስ በዕርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባሕል እንዲጎለብት አድርገናልም ነው ያሉት።

ልበ-ቀና ባለሀብቶች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በማድረግ በከተማችን ማኅበራዊ ፍትህ ለማንገስ በትጋት ሰርተናል ሲሉም ገለጸዋል።

በበጎነት ከጎናችን የቆማችሁ ወጣቶች፣ ልበ-ቀና ባለሀብቶች፣ የመንግስትና የግል ተቋማት ሰራተኞችና የከተማችን ነዋሪዎች ስለቀና ልባችሁና ስላደረጋችሁት በጎነት ሁሉ በነዋሪዎቻችን ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል።

በበጎነትና በትጋት እያገለገልን ከተማችንን ከፍ እናደርጋለንም ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.