ኢትዮ ቴሌኮም ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች ተንቀሳቃሽ ሱቆችን አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች ተንቀሳቃሽ ሱቆችን አበረከተ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና ሌሎችም የኩባንያው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተንቀሳቃሽ ሱቆቹ ርክክብ ተደርጓል።
በ8 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የተሰሩ 30 ተንቀሳቃሽ ሱቆች ለ99 ወጣት ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ተበርክተዋል።
ኩባንያው የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ 26 የበጎ አድራጎት ማዕከላት ለሚገኙ 7 ሺህ አረጋውያን ማዕድ አጋርቷል።
በተጨማሪም ለ70 ሺህ ተማሪዎች 840 ሺህ ደብተሮችን ለመለገስ መዘጋጀቱን ኢዜአ ዘግቧል።
የበጎነት ቀን “በጎነት ለሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ መርሐ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።