ቢዝነስ

ኋ ጂየን ጫማ ፋብሪካ ከ8 ሺህ ለሚልቁ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል ፈጠረ

By Alemayehu Geremew

September 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአምራችነት ፈቃድ አግኝቶ የተከፈተው የቻይናውያኑ ኋ ጂየን ጫማ ፋብሪካ ከ8 ሺህ በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገለጸ፡፡

መሠረቱን ቻይና ያደረገው “ኋ ጂየን ግሩፕ” በጫማ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስ ከጀመረ 12 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

የኩባንያው አማካሪ ቃሉ ከበደ እንዳሉት ምርቶቹን ከኢትዮያ አልፎ ለአውሮፓ፣ አሜሪካ እና አፍሪካ ገበያ ለማቅረብ እየሰሩ ነው፡፡

በተጨማሪም የጫማ ፋብሪካው በቀጣይ ንግዱን ወደ ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ለማስፋት ፍላጎት አለው ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡