“የአብሮነት ቀን” በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጷጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጷጉሜን 6 “የአብሮነት ቀን” በተለያዩ መርሐ ግብሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡
የጷጉሜን 6 የአብሮነት ቀን”“በህብር የተሰራች ሀገር”በሚል መሪ ሀሳብ ነው በመንግሥት እና በግል ተቋማት እየተከበረ የሚገኘው፡፡
የቀኑ መከበርም የአብሮነት እሴትን ለማጎልበት፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና አንድነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል፡፡