Fana: At a Speed of Life!

የአብሮነት ቀን በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጳጉሜን 6 የአብሮነት ቀን በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡

የአብሮነት ቀን “በህብር የተሰራች ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ  ይገኛል፡፡

በክልሉ የተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች በዓሉን በማስመልከት ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአብሮነት ቀን በእግር ጉዞ እና በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡

የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በ2015 ዓ.ም የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጥረት ሲደረግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋን የሰላምና የመቻቻል እንዲሁም የአብሮነት መገለጫነትን ወደፊትም ለማስቀጠል እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በሀረሪ ክልል የአብሮነት ቀን የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም እና የሀረሪ ጉባኤ አፈጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ እንዲሁም የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ በተገኙበት ተከብሯል።

በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ÷ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት በመከባበር በመተባበርና አብሮ በአብሮነት የኖሩ ህዝቦች ናቸው ብለዋል።

በተለይም ምሳሌ የሆነው የክልሉ ህዝብ አብሮ የመኖር እሴት ተጠብቆ እንዲቆይ ማድረግ የዚህ ትውልድ ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመው ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይገባል ነው ያሉት።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.