Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ድርጅቶች ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ለኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚውል ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተለያዩ ድርጅቶች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
 
ለኮቪድ19 መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጅት የሚውል ገንዘብ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ለማሰባሰብ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ደርጅቶቹ ድጋፋቸዉን ለብሔራዊ ድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ በትናትናው ዕለት አስረክበዋል፡፡
 
በዚህም የኢትዮጵያ መድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች አምራቾች ማህበር 2 ሚሊየን 800 ሺህ ብር በገንዘብ እና 7 ሚሊየን 247 ሺህ ብር ግምት ያላቸዉ የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
በተመሳሳይ ኢትዮ ሊዝ የኢትዮጵያ የካፒታል ዕቃዎች ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር 1 ሚሊየን 680 ሺህ ብር ፣ ዛብሎን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ 1 ሚሊየን ብር እና የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም አክሲዮን ማህበር 500 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
በአጠቃላይ በትናትናው ዕለት 5 ሚሊየን 980 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም 7 ሚሊየን 247 ሺህ ብር የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ መደረጉን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.