Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ1 ቢሊየን ብር የግብር እዳ ምህረት አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከ21 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ግብር ከፋዮች የ1 ቢሊየን ብር የግብር እዳ ምህረት ማድረጉን አስታወቀ።

ምህረቱ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የግብር ግዴታቸውን ያልተወጡ ግብር ከፋዮችን ተጠቃሚ ያደርጋልም ነው የተባለው።

በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በኢኮኖሚው ላይ የሚደርሰውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የታክስ እዳ ምህረት መደረጉን የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን ተናግረዋል።

በዚህም ከ2007 ዓ.ም እስከ 2008 ዓ.ም ከ7 ሺህ በላይ ለሆኑ ግብር ከፋዮች 288 ሚሊየን ብር ምህረት ተደርጓል ነው ያሉት።

በተጨማሪም ከ2008 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ደግሞ ከ14 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች 784 ሚሊየን ብር የግብር እዳ ምህረት እንደተደረገላቸው ገልጸዋል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.