Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ማዕድ የማጋራት መርሐ  ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደሴ፣ ጎንደር፣ ባሕር ዳርና ወልዲያ ከተሞች የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

በባህር ዳር እና በወልዲያ ከተሞች አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሐ-ግብር ተከናውኗል፡፡

ከመርሐ ግብሩ ውስጥ የባህር ዳር በጎ አድራጎት ማህበር ለ5 ሺህ 350 አቅመ ደካሞች፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች የተከናወነው ማዕድ ማጋራት አንዱ መሆኑን የዘገበው ኢዜአ ነው።

እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ጨምሮ ሌሎች የጸጥታ አካላት የዘመን መለወጫ በዓልን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደሴ ከተማ አክብረዋል፡፡

በዚህ ወቅት ብርጋዴር ጀነራል ዘውዱ ሰጥአርጌ÷ ሰራዊቱ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡

በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አመራሮች እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲሁም መሪዎች የአዲስ ዓመት በዓልን በጋራ አክብረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.