Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የ40 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የ40 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ልታደርግ ነው።

የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ፍሪዴሪክ ቦንቴምስ ድጋፉን ይፋ አድርገዋል።

ድጋፉ ኢትዮጵያ ኮቪድ19ኝን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ታሳቢ ባደረገ መልኩ በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ በኩል የሚለቀቅ ነው ተብሏል።

የሚለቀቀው ድጋፍ መንግስት የአጭር ጊዜ ችግሮችን ለመቅረፍ እና አስቸኳይ እቅዶቹን ለመተግበር የሚያደርገውን ጥረት በተለይም በሃገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የኢኮኖሚ ሽግግር ለማሳካት ያግዛል ነው የተባለው።

የአሁኑ ገንዘብ ፈረንሳይ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ የምትሰጠው የ85 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አካል ነው ተብሏል።

የድጋፍ ስምምነቱ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፈው የፈረንጆች አመት በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መፈረሙ የሚታወስ ነው።

የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ከ500 ሚሊየን ዩሮ በላይ ፈሰስ ማድረጉን ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.