በአዲስ አበባ በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የአረጋውያን መጠለያ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የአረጋውያን መጦሪያ፣ መጠለያና እንክብካቤ ማዕከል ተመረቀ፡፡
ማዕከሉ ለ730 አረጋውያን እንክብካቤ የማድረግ አቅም አለው መባሉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ማዕከሉ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮች፣ ፋርማሲ፣ ምግብ ማብሰያ፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ መኝታ ቤት፣ የልብስና የአረጋውያን ንፅህና መጠበቂያ፣ የዕደ- ጥበብ መስሪያ እና የመዝናኛ ቦታዎችን ያከተተ መሆኑም ተጠቅሷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሥነ – ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ “ቀደምቶቻችንን ለዋሉት ውለታ አመስግነን ስንንከባከባቸው መጪው ትውልድ ይበረታል” ብለዋል፡፡
ለማዕከሉ በቋሚነት ገቢ ማስገኛ የሚሆን ባለ ሶስት ወለል ሕንጻ መኖሩንም አንስተዋል፡፡
አዲስ አበባ ለሁሉም ምቹ እንድትሆን ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ባለሀብቶች ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መሥራት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዛሬ የተመረቀው ማዕከልም በ630 ሚሊየን ብር የሰንሻይን ፊላንት ሮፒ ፋውንዴሽን ግንባታውን በጥራት በማጠናቀቅ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ስለተወጣ እናመሰግናለንም ነው ያሉት ከንቲባዋ።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!