ስፓርት

አርቢትር ባምላክ ተሰማ የ2024 አፍሪካ ዋንጫን ከሚመሩ ዋና ዳኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

By Amele Demsew

September 14, 2023

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 3 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የኮትዲቯሩን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞችን ዝርዝር ይፋ አድርግል።

በዝርዝሩ የመሀል፣ ረዳት፣ የቪዲዮ ረዳት ዳኞች፣ ቴከኒካል ኢንስትራክተሮች፣ የVAR ቴክኒሻኖች እና የአይቲ ባለሙያዎች ተካተዋል።

85 ባለሙያዎች ይፋ በሆኑበት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የአፍሪካ ዋንጫን ከሚመሩ ዳኞች አንደኛው ሆነው ተካተዋል።

በዝርዝሩ ከ26 ሀገራት 32 ዋና ዳኞች የተመረጡ ሲሆን፥ አርቢትር ባምላክ ተሰማ ኢትዮጵያን ወክለው በዝርዝሩ መካተታቸውን ካፍ አስታወቋል።