Fana: At a Speed of Life!

የሳይነስ አጋላጭ ምክንያቶች ምንድናቸው?

 

 

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳይነስ በአፍንጫ ሰርን፣ በአይን መካከል እና ግምባር ውስጥ የሚገኙ ህብረ ህዋሳት በሚያብጡበት ጊዜ የሚፈጠር ህመም ነው፡፡

 

የሳይነስ መንስዔዎች ወይም አጋላጭ  ምክንያቶች ምንድናቸው?

 

የሳይነሳይተስ በሽታ በቫይረስ፣ በባክቴሪያ ወይም በፈንገስ ሊከሰት ይችላል ከዚህ ባለፈም ጉንፋን፣ ወቅትን ጠብቆ የሚከሰት አለርጂ ፣ የአፍንጫ  ውስጥ ዕጢዎች ፣ የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ፣ጨቅላ ህጻናትን እና ትንንሽ ልጆችን ተኝተው አልያም ተንጋለው ጡጦ ማጥባት  እና ሲጋራ ማጨስ ለሳይነሳይተስ ሊያጋልጡን ይችላሉ።

 

ምልክቶቹ  ደግሞ ከአፍንጫ ኋላ የሚያልፍ ንፍጥ ፣ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ (ወፍራም ቢጫ  ወይም አረንጓዴ) ፣የአፍንጫ መታፈን፣የፊት ላይ ግፊት (በተለይ በአፍንጫ፣ በአይን እና በግንባር አካባቢ)፣ ራስ ምታት፣ የጥርሶች ወይም የጆሮ  ህመም፣ ሃሊቶሲስ (መጥፎ የአፍ ጠረን) ፣ ሳል፣ ድካም፣ እና ትኩሳት መሆናቸውንየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.