Fana: At a Speed of Life!

የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳ 2030ን እና 17ቱን ዘላቂ የልማት ግቦች አጀንዳ አድርጎ ይመክራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)78ኛው የተመድ ጠቅላላ የመሪዎች ጉባዔ የፊታችን ሰኞ አሜሪካ ኒውዮርክ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ይጀመራል፡፡

በመጀመሪያው ግንኙነታቸው የዓለማችን መሪዎች እና መንግሥታት አጀንዳ 2030ን እና 17ቱን ዘላቂ የልማት ግቦች አፈጻጸም ይገመግማሉ ተብሏል፡፡

ከግምገማቸው በኋላም ሊወሰዱ የሚገባቸውን ማስተካከያዎች እና አፋጣኝ እርምጃዎች ላይ ውሳኔዎች እና ከፍተኛ ፖለቲካዊ መመሪያዎች ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጉባኤው ከማክሰኞ ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ መስከረም 23 ቀን ድረስ ለአምሥት ቀናት ይካሄዳል።

በዚህ ወቅትም መሪዎቹ “ዓለምአቀፋዊ መተማመንን እና ትብብርን ማደስ እንዲሁም አጀንዳ 2030 እና ዘላቂ የልማት ግቦቹን ተግባራዊነት ለማፋጠን ስለሚወስዷቸው ዕርምጃዎች በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

የልማት ግቦቹ የዓለማችን ሀገራት ወደ ዘላቂ ሠላም እና ብልፅግና የሚያደርጉትን ጉዞ የሚመሩ መሆናቸው ይታመናል፡፡

በጉባዔው የልማት ግቡን በገንዘብ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመከርም ተመድ በመርሐ-ግብሩ ዝርዝር ላይ አመላክቷል፡፡

በአዲስ አበባ የድርጊት መርሐ-ግብር አጀንዳ ላይ ተመድ ያስቀመጣቸውን የልማት ግቦች ለማሳካት ስለሚወስዷቸው ፖለቲካዊ ውሳኔዎች እና አፈጻጸሞች ይመክራሉ ፣ ግብዓት ያሰባስባሉ ፣ መመሪያም እንደሚያወጡ የተመድ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.