Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ ከካናዳ አለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ጋር መከሩ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ ከካናዳ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ቼሪል አርባን ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምሥጋኑ ከቼሪል አርባን ጋር በኢትዮጵያ እና በካናዳ መካከል ያለውን ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ አምባሳደር ምሥጋኑ÷ ካናዳ ለኢትዮጵያ ለምታደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ጠንካራ አጋርነት አድናቆታቸውን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በርካታ ስደተኞችን ተቀብላ የምታስተናግድ ሀገር እንደመሆኗ መጠን እና በቀጣናው ያላትን ሚና ከግምት በማስገባት እንዲሁም እያስመዘገበች ካለችው እድገት አንጻር ካናዳ ድጋፏን ማጠናከር እንደሚገባት በውይይታቸው አንስተዋል።

ሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብራቸውን በማጠናከር የሀገራቱን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማሳደግ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.