Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አመራሮችና አባላት ዕውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አመራሮችና አባላት ዕውቅና ሰጠ።

በመርሐ-ግብሩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት እውቅና የተሰጣቸው በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ ሥር እንዲሁም በዋና መሥሪያ ቤት የሚገኙ የሥራ ክፍሎችና ለኮሚሽነር ጄኔራል ተጠሪ የሆኑ መምሪያዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራልና የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ኅብረት ፕሬዚዳንት ደመላሽ ገብረሚካኤል እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በተመሳሳይ ለአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ምህረት ደበበ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የክብር አምባሳደርነት መታወቂያ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል ነብዩ ዳኜ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የፌዴራል ፖሊስ መጠነ ሰፊ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራ አከናውኗል።

በዚህም ፌዴራል ፖሊስ ተልዕኮውን መወጣት የሚያስችለው አቅም መፍጠሩን ገልጸው÷ ጠቅላይ መምሪያው ባከናወነው የመፈጸም አቅምን የማሳደግ ሥራ የወንጀል መከላከል አድማስ እንዲሰፋ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች ሀገራት እንዲሁም አኅጉራዊ ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.