የ2016 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 እና 27 ይከበራል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 27 በሆረ ሀርሰዲ እንደሚከበር ተገለጸ፡፡
የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ጸሐፊና የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ በሰጡት መግለጫ÷ ኢሬቻ የምሥጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በመሆኑም ሕረተሰቡ ወደ ማክበሪያ ቦታው ሲመጣ የባሕል አልባሳትን በመልበስ እንዲገኝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኦሮሞ ማንነትና አንድነት መገለጫ በሆነው በዓል ላይ የሚሳተፉ ሁሉ በዓሉን በሥነ- ምግባሩና በሥርዓቱ እንዲያከብሩ አሳስበዋል።