Fana: At a Speed of Life!

የተመድ 78ኛው ጉባዔ በሩሲያና ዩክሬን ጉዳይ ላይ በስፋት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በዚህ ሣምንት በሚያካሂደው 78ኛው ጉባዔ በሩሲያና ዩክሬን ጉዳይ እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ላይ በስፋት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

78ኛው የተመድ ጠቅላላ የመሪዎች ጉባዔ አሜሪካ ኒውዮርክ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው የሚነሱ ሐሳቦች ሀገራት በመጪው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ቅድሚያ ሰጥተው በሚሠሯቸው ሥራዎች ላይ ዕቅዶቻቸውን እንዲያስተካክሉ አቅጣጫ ያመላክታቸዋልም ተብሏል፡፡

ምናልባትም ሀገራት በአስቸጋሪ ጉዳዮቻቸው ላይ እንዲተባበሩ ወይም አቋም ይዘው ጎራ እንዲለዩ በአንድ የሚያገናኛቸው መድረክ እንደሚሆን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ከጉባዔው ጎን ለጎን ሀገራት የሁለትዮሽ ውይይቶች ይኖራቸዋል፡፡

የዘንድሮው አጠቃላይ የክርክር መድረክ÷“ዓለም ዓቀፋዊ መተማመንን እና ትብብርን ማደስ፤ ወደ ዓለም ዓቀፋዊ ሠላም፣ ብልፅግናና ዕድገት በሚያደርሰው አጀንዳ 2030 በመወያየት ዘላቂ የልማት ግቦቹ ተግባራዊነት ላይ የጋራ ጭብጥ መያዝ” በሚለው መሪ-ሐሳብ ላይ ያተኩራል፡፡

በጉባዔው ከ140 በላይ ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.