አሜሪካ የጠፋባትን ኤፍ -35 የጦር ጄት እየፈለገች ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የጠፋባትን ኤፍ -35 ተዋጊ የጦር ጄት መፈለግ ጀምራለች፡፡
በደቡብ ካሮላይና የሠፈሩት የአሜሪካ አየር ኃይል ጦር አባላት ሕዝቡ ጄቱን ወይም ስብርባሪውን በማፈላለግ ረገድ እንዲተባበሯቸው ጠይቀዋል።
ትናንት ከሠዓት ጄቱን ሲያበሩ የነበሩት ፓይለት አደጋው ከመድረሱ በፊት ሰሜን ቻርለስተን ላይ በፓራሹት በመውረድ ነፍሣቸውን ማትረፋቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
አብራሪው መሬት ካረፉ በኋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን እና በመልካም ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ወታደራዊ ቃል አቀባይ የሆኑት ሜጀር ጀኔራል ሜላኒ ሳሊናስ ተናግረዋል፡፡
እስካሁን ጄቱን አየሁ የሚል አንድም ሰው አልተገኘም፡፡
ጄቱን በማፈላለጉ የሚመለከታቸው አካላት ሁለት ሐይቆች አካባቢ ያሉ ቦታዎችን ትኩረት አድርገው እየፈለጉ ነው ተብሏል።