በትግራይ ክልል ነገ መደበኛ ትምህርት ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት ነገ እንደሚጀመር የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የ2016 የትምህርት ዘመንን ነገ ለማስጀመር ለትምህርት ማሕበረሰቡ ሥልጠና መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡
በዚህም ባለፉት 5 ቀናት ለመምህራን እና ለትምህርት ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን ነው የገለጸው፡፡
ስልጠናው እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም ቢሮው ምስጋና አቅርቧል፡፡
በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ በየአካባቢው የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ቢሮው ጥሪ አቀርቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!