Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ሱዝማን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያና በፋውንዴሽኑ መካከል ያለው ግንኙነት የሚደነቅ እንደሆነ ገልጸዋል።

የፋውንዴሽኑ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ ሰላምን ለማጠናከር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያጠናክርና የ10 ዓመቱን የልማት ዕቅድ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገቱን እያስቀጠለ እንደሚገኝ አመልክተው፤ የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ያለው ስራ ሀገራዊ ዋና ፕሮጀክት እንደሆነ ገልጸዋል።

ከልማት አጋሮች ጋር ያለው ተስፋ ሰጪ የሆነ የሁለትዮሽና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ኢትዮጵያ አጠናክራ እንደምትቀጥልበት አስገንዝበዋል።

የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ሱዝማን በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በጤና፣ በግብርና፣ በዲጂታል ፋይናንስና በሌሎች ዘርፎች ጠንካራ አጋርነት እንዳለው ጠቅሰዋል።

ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ የልማት ግቦች ጋር የተናበቡ ተግባራትን ማከናወኑን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ የመሪዎች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.