Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 67 አዳዲስ አውቶቡሶች ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እጥረቱን ለመቅረፍ ተጨማሪ አዳዲስ 67 የከተማ አውቶቡሶች በቀጣይ ወር ወደ ስምሪት እንደሚገቡ የአዲስአበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

አውቶቡሶቹ ከውጭ ሀገር መገዛታቸውን እና አሁን ላይም በባሕር ትራንስፖር የጉዞ ሂደት ላይ መሆናቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዳዊት ዘለቀ (ኢ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩትን እና ጥገና የተደረገላቸውን ጨምሮ 1 ሺህ 100 ተሽከርካሪዎች ወደ ስምሪት መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቡሶች የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ሌሎች 100 የሚደርሱ አውቶቡሶች ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ እና ከማዕከል ጥገና ተደርጎላቸው በቀጣይ ወደ ስምሪት እንደሚገቡ አመላክተዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.