Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ-ቴሌኮም የምዕራብ ሪጅን በ5 ሚሊየን ብር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮም ምዕራብ ሪጅን በአራቱም የወለጋ ዞኖች ለሚገኙ የአቅመ ደካማ ተማሪዎች እና ለተፈናቃይ ወገኖች የ5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የተቋሙ የምዕራብ ሪጅን ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ አስረስ ብርሃኑ÷ህፃናት ከቁሳቁስ እጥረት የተነሳ ሳይማሩ እንዳይቀሩ የበኩሉን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ተቋሙ 5 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተፈናቃይ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እንዲሁም የ375 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ እንዳደረገ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.