Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትን የመከላከል ጥረት የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አልቻለም ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት ባለፉት አመታት ከነበረበት የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም የሚፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት አለመቻሉ ተገለፀ፡፡

በክልሉ ዓመታዊ የኤችአይቪ/ኤድስ የመከላከልና የመቆጣጠር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና በቀጣይ የስራ ዕቅድ ዙርያ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ÷ በክልሉ የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት 3 ነጥብ 6 በመቶ አካባቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ባለፉት አመታት ከነበረበት የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም የሚፈለገውን ያህል ውጤት ግን ማምጣት አለመቻሉንም መናገራቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ኡቶው አኳይ በበኩላቸው÷ በክልሉ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት ሁሉም እንዲረባረብ ጠይቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.