Fana: At a Speed of Life!

ህንድ የካናዳ ዲፕሎማት በ5 ቀናት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ የካናዳ ከፍተኛ ዲፕሎማት በ5 ቀናት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፏን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ህንድ ትዕዛዙን ያስተላለፈችው በካናዳ “የሲክ“ ተገንጣይ በመገደሉ እየተባባሰ በመጣው አለመግባባት ምክንያት ኦታዋ አንድ የህንድ ዲፕሎማትን ከሀገሯ ማባረሯን ተክትሎ ነው፡፡
የህንድ ውሳኔ የካናዳ ዲፕሎማቶች በውስጥ ጉዳያችን ላይ የሚያደርጉት ጣልቃገብነትና በፀረ-ህንድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያሳይ ነው ሲል ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ችግሩ በካናዳና በህንድ ግንኙነት መካከል ውጥረት ያነገሰ ሲሆን÷ ይህንንም ተከትሎ የንግድ ድርድሮች መቋረጥ እና ካናዳ በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ወደ ህንድ ልታደርግ የነበረውን የንግድ ተልዕኮ ዕቅድም እንድትሰረዝ አድርጓታል።
በካናዳ የሲክ ቡድኖች ያካሄዱት ተቃውሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ መንግስትን አስቆጥቷል።
ካናዳ በፈረንጆቹ 2023 ሰኔ ወር ላይ በብሪቲሽ ኮሎምቢያ ሱሬይ የባህል ማዕከል ደጃፍ የሲክ ተገንጣይ መሪ ሃርዲፕ ሲንግ ኒጃር ላይ ከተፈጸመ ግድያ ጋር የህንድ መንግስት ወኪሎች እጅ አለበት በሚል ከሳለች፡፡
ህንድ በበኩሏ የካናዳን ክስ ውድቅ ያደረገች ሲሆን÷ ከዚህ ይልቅ በሀገሯ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ህንድ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንድትወስድ ማሳሰቧን አልጀዚራ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.