የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የተሰራው የመታሰቢያ ሐውልት በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዛሬ ተመርቋል።
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የተለያዩ መጻሕፍትን በመጻፍ የኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ፈር ቀዳጅ ሲሆኑ÷ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነውም አገልግለዋል።
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉና የልዩ ፍርድ ቤት ዳኛም በመሆን ሀገራቸውን እንዳገለገሉ ተገልጿል።
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽን የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ልዑክ አባል በመሆን ማገልገላቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በሀውልት ምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተወካዮች፣ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ተመራማሪዎች እና ደራሲያን፣ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ወዳጅ ዘመዶችና ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!