Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ዳያስፖራዎች የውይይት መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይና የፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ጠይብ አሕመድ፣ የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ዘይነብ ሀጂ አደን እንዲሁም የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ተገኝተዋል።

በክልሉ በየአመቱ የሚካሄደው የክልሉ መንግስትና የዳያስፖራዎች ውይይት መድረክ “የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች የክልሉ ልማት የጀርባ አጥንት ናቸው” በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው፡፡

በክልሉ ልማትና በተለያዩ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ዳያስፖራው ተሳታፊ በሚሆንበት ሁኔታ ላይም ምክክር መካሄዱ ተገልጿል፡፡

የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በትምህርት፣ በግብርና፣ በእንስሳት ልማት፣ በኢንዱስትሪ ልማትና በሌሎች በክልሉ በሚገኙ የልማት ስራች ላይ እንዲሰማሩም ጥሪ መቅረቡን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.