የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካናዳ የበረራ አድማሱን ለማስፋት የሚያስችለው ምክክር ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አድማሱን በካናዳ ለማስፋት እንዲችል ውይይት ተደርጓል፡፡
ምክክሩ ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የሚመራው የልዑካን ቡድን ከካናዳ አየር መንገድ ዋና ተደራዳሪ ሸንድራ ሜሊያ እና ተደራዳሪ ቡድናቸው ጋር የተደረገ ነው፡፡
በአምባሳደር ምስጋኑ የተመራው የልዑካን ቡድን በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን እንዳካተተ ተገልጿል፡፡
ይህንን ጉዳይ የበለጠ ለመፈተሽ በማሰብም ሁለቱ ወገኖች የሚያደርጉትን ምክክር ለመቀጠል መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopia #Canada #ethiopianairlines
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!